በሆሳእና ከተማ በእሳት አደጋ 3 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

59
ሆሳዕና የካቲት 15/2012 (ኢዜአ) በሆሳእና ከተማ በተከሰተ የእሳት አደጋ ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን የከተማው ፖሊስ ገለፀ ፡፡ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታምራት እሼቱ ለኢዜአ እንደገለጹት በከተማው በተለምዶ ዋንዛ ሰፈር በተባለው አካባቢ ትናንት ከሌሊቱ 7 ሰዓት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል ። የአደጋው ምክንያት አለመታወቁን የገለፁት አዛዡ በእሳት አደጋው አንድ የእንጨት ማምረቻ ድርጅት ከነ ሙሉ የማምረቻ መሳሪያዎቹና ለሽያጭ የተዘጋጁ ምርቶቹ ጭምር ወድመዋል ። የአደጋው መንስኤ  ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑን ኢንስፔክተር ታምራት ገልፀው፤ ህብረተሰቡ እሳት ሊፈጥሩ የሚችሉ ስራዎችን ሲያከናውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልእክት አስተላልፈዋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም