ፕሬዝዳንት አል ሲ ሲ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ የተላከ ልዩ ልዑክ ተቀብለው አነጋገሩ

56
የካቲት 15/2012 ኢዜአ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ልዩ ልዑክ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ። በልዑካን ቡድኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁንና በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ መካተታቸው ተገልጿል። በውይይቱም በታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ የተገኙ ለውጦች በተመለከተም መነጋገራቸው ተመልክቷል። ኢትዮጵያና ግብጽ ስላላቸው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነትም በውይይቱ ተነስቷል። በቀጣይም ይህ ግንኙነት ለማጠናከር የሚቻልባቸው መንገዶች ላይም መክረዋል። ልዩ ልዑካን ቡድኑ ግብጽ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በነበረችበት ወቅት የፕሬዝዳንት አል ሲ ሲ  አመራር ማድነቁም ተጠቅሷል። ምንጭ- ( በካይሮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም