በጣሊያን 62 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

100

የካቲት 15/2012 (ኢዜአ) በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 62 መድረሱን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

በደቡብ ኮሪያ በ48 ሰአታት ውስጥ 350 አዳዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ይህም አጠቃላይ ቁጥሩን 550 ማድረሱ ተመልክቷል።

በዘገባው እንደተመለከተው ቫይረሱ በመካከለኛው ምስራቅ አገራትም እየተስፋፋ ይገኛል።

የኢራን የጤና ሚኒስቴር 28 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን  አረጋግጧል።

ሌባኖስ እና እስራኤልም በአገራቸው በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን አስታውቀዋል።

የአለም የጤና ድርጅት ጀነራል ዳይሬክተር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመገደብ ያለው ዕድል እየጠበበ መምጣቱንና አገራት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።

በአለም አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 461 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር  79 ሺህ 930 መድረሱን ከሲ ኤን ኤን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም