የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ መርሃ ግብር በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው

64
የካቲት 15/2012 (ኢዜአ) የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማብሰሪያ መርሃ ግብር በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው።
ለአገር አቀፍ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት መርሃግብሩ የሚሳተፉ ከየክልሉ የተወጣጡ ወጣቶች ታድመዋል።
'በጎነት ለአብሮነት' በሚል መሪ ሀሳብ በሰላም ሚኒስቴር በተዘጋጀው መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል። ለአገልግሎቱ አምስት የበጎ ፈቃድ አምባሳደሮች ተመርጠዋል፤ ከመላ አገሪቷ የተውጣጡ ከ116 ሺህ በላይ ወጣቶችም ተመዝግበዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የሚሰጠው መንግስታዊ ካልሆኑ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሆነም ተገልጿል። መርሃ ግብሩ የዜጎችን አብሮ የመኖር እሴት ያዳብራል። 10 ሺህ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በመጀመሪያው ዙር ለሁለት ወራት እንደሚሰለጥኑ ታውቋል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የሚሳተፉ ወጣቶች ከሚያገኙት እርካታ በተጨማሪ በተለያዩ ተቋማት መቀጠር የሚያስችላቸው የስራ ልምድ ይሰጣቸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም