በአዳማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

90
አዳማ  የካቲት 15/ 2012 (ኢዜአ) የአዳማ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ለውጡን በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው:: የአዳማ ከተማና አካባቢው  ነዋሪዎች ለውጡን በመደገፍ ዛሬ ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምረው ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ በማካሔድ ላይ ናቸው ። ሰልፈኞቹ በትግላችን ያመጣነውን ለውጥ እንጠብቃለን  እንከባከባለን !  ለለውጡ ውጤታማነት የድርሻችንን እንወጣለን !  የሚል መፈክር አንግበው ወደ አዳማ መስቀል አደባባይ በማምራት ላይ ናቸው ። መነሻችን መደመር መድረሻችን ደግሞ ብልፅግና ነው !  ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በመጠበቅ ለውጡን ከዳር እናደርሳለን ! የሚሉ መፈክሮችም ሰልፈኞቹ ከሚያስተጋቡዋቸው መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ። የሰልፉ ተሳታፊ ህዝብ ቁጥር ከ70 ሺህ በላይ መሆኑን በቦታው የሚገኙ የኢዜአ ሪፖርተሮች የዘገቡ ሲሆን በአዳማው መስቀል አደባባይ የኦሮሚያ ክልል  ፣ የምስራቅ ሸዋ ዞንና የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም