የቀድሞ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች መሪ ማቻር ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

71
የካቲት  14/2012 የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተቃዋሚያቸው የነበሩት ሬክ ማቻርን የሀገሪቷ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡ የተቃዋሚው ቡድን መሪው ሪክ ማቻር ሹመት የተሰማው ሁለቱ አካላት የብሄራዊ አንድነት መንግስት ለመመስረት ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የነዳጅ ሀብት ያላት ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ 2011 ጎረቤት ሰሜን ሱዳን ነፃነቷን ካገኘች ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር እርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው ፡፡ ግጭቱ በ 1994 በሩዋንዳ ከተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወዲህ 400,000 ያህል ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈና ትልቁን የስደተኛ ቀውስ ያስከተለ ነበር ተብሏል፡፡ ግጭቱ የተፈጠረው በዛን ወቅት የሳልቫኬር ምክትል በመሆን በስልጣን የነበሩት ማቻር ከስልጣን መውረዳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘገባው ያመለክታል፡፡ ምንጭ፡-ሲጂቲኤን አፍሪካ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም