የሶማሊያ እና አሜሪካ ጥምር ጦር በፈፀሙት የአየር ድብደባ 3 የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

58
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12/2012 (ኢዜአ) የሶማሊያ እና አሜሪካ ጥምር ጦር በሞቃዲሾ አቅራቢያ በምትገኘው ዋዳጂር አካባቢ በፈፀሙት የአየር ድብደባ ሶስት የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን አስነበበ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ እዝ በምህፃሩ አፍሪካኖም እንዳስታወቀው ከሆነም ጉዳት የደረሰበትም ሆነ የሞተ ንፁሃን ዜጋ የለም ብሏል፡፡
የአፍሪኮም ደህንነት ምክትል ዳይሬክተሩ ግሪጎሪ ሃደፋልድ እንዳሉትም ባለፉት ጊዚያት የሚፈፀሙ የአል-ሸባብ ጥቃቶች በተሻሻሉ ፈንጂ መሳሪያዎችና ተሸከርካሪም ጭምር በመታገዝ የአጥፍቶ ጠፊነት ተግባርም ይፈፀም ነበር ብለዋል፡፡ የሶማሊያን መንግስት ለማጠናከር በሚል እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ በአፍሪቃ ህብረት እና የአሜሪካ ጥምር ጦር የአል-ሸባብን ሽምቅ ተዋጊ ለማጥፋት በአየርና ምድር ጥቃት እያደረገ እንደሚገኝም ሲ ጂ ቲ ኤን በአፍሪካ ገፅ ዘገባው አስፍሯል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም