የካቲት 10/2012 (ኢዜአ)ይህ የገንዘብ ዝውውር እ.እ.አ በ 2019 የተደረገ ሲሆን የሀገሪቱ የሞባይል ባንኪንግ ደንበኞች ቁጥርንም ማደጉን የሚያሳይ ነው ተብሎለታል፡፡
ዝውውሩ በተለያዩ የሞባይል ባንኪንግ ማስተላለፊያ ዘዴዎች የተከናወነ ሲሆን ታንዛንያን በአፍሪካ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ እንቅስቃሴ ካደረጉ ሀገራት ተርታ አስመድቧታል፡፡
ይህም ለታንዛንያ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን የጥሬ ገንዘብ ልውውጥን አስቀርቶ ቀስ በቀስ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክፍያ ዘዴን አስፋፈቷል፡፤
በዚህም ታንዛናውያንን ከመደበኛው የባንክ አጠቃቀም ወደ ቀልጣፋው የገንዘብ ዝውውር ተሸጋግረዋል፡፡
የታንዛንያው የሞባይል ማዘዋወሪያ አሁን ላይ ተደራሽነቱን ከ 46 በመቶ ወደ 85 በመቶ ከፍ ያደረገ ሲሆን በ 2014 አስር ሚሊዮን አዲስ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ለማፍራት እቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ፡፡
የሞባይል ባንኪንግ ስርአት በአሁኑ ሰአት ከመደበኛው ስርአት ቀላል እና ቀልጣፋ ማስተላለያ ዘዴ ሲሆን ተጠቃሚዎች ለሚያስፈልጓቸው እንቅስቃሴዎች ቀላል አገልግሎት የሚያገኙበት አጋጣሚ ነው ሲል ሪፖርቱ ጠቅሶ ኦል አፍሪካ ዘግቧል ፡፡