አማዞን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የአስር ቢሊዮን ዶላር ሰጠ

64

የካቲት  ኢዜአ 10/2012 አማዞን የአየር ንብረት ለውጥ  ለመከላከል  የአስር ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ  አደረገ፡፡

የአማዞን መስራችና ዋና ስራ አሰፈጻሚ ጄፍ ቤዞስ በአለማችን ምቹ  አየር ሁኔታ ለመፍጠር  ለሚደረገው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ተቋማቸው  የአስር ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ጄፍ ቤዞስ 1.4 ሚሊዮን ተከታይ ባለው የኢኒስተጋግራም ገጻቸው እንደገለጹት ድጋፉ ለአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ለሚሰሩ ተመራማሪዎች፣ ተሟጋቾች፣መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት የሚውል ነው ብለዋል፡፡

የአየር ንበረት ለውጥ ለአለማችን ትልቁ ስጋት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው በቀጣይ ይህንን ችግር ለመቅረፍ አማዞን ተሳትፎውን አንደሚያሳድግም ተናግረዋል፡፡

አማዞን በአየር ንብረት ዙሪያ  አልሰራም በሚል  በተለያዩ አለም አቀፍ አካላት እና የመብት ተሟጋቾች ክስ የሚቀርብብት ሲሆን ባሳለፍነው ወር  በተቋሙ  የሚሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በኦን ላይን የብሎግ ገጾች በኩል የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር፡፡ የዜናው ምንጭ ካፒታል ኤፍኤም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም