የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተጀመረ

162
ባህርዳር፤ የካቲት 10/2012 የአማራ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ጀመረ። የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ትልቅ ሰው ይታያል በምክር ቤቱ የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳሉት በአስፈፃሚው አካል ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ክትትል ይደረጋል። በተለይም የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸው ወቅታዊና የቆዩ ጥያቄዎች እንዲፈቱ የምክር ቤቱ አባላት የተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ተናግረዋል። የዛሬው አስቸኳይ ጉባኤም የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት በቀጣይ የምክር ቤት አባላቱ የወከላቸውን ህዝብ እንዴት ማግኘትና ማወያየት እንዳለባቸው አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም