በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድሮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

53
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 9/2012 በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ እየተደረጉ ባሉ የሶስትዮሽ ድርድሮች ላይ ያተኮረ ውይይት በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተካሄደ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ላይ ሚኒስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ የቴክኒክ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ባለ ድርሻ አካላትና የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። የውይይት መድረኩም ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ባሉት የሶስትዮሽ ድርድሮች አካሄድና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው። ኢትዮጵያ፣ ከግብዕና ከሱዳን ጋር በግድቡ የውሃ አለቃቀቅና አሞላል ዙሪያ በአሜሪካ በዋሽንግተን ስታካሂደው በነበረው ድርድር ብሔራዊ ጥቅሟን የሚነካ በመሆኑ አቋርጣ መውጣቷ ይታወቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም