ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተደረሰባቸው 3 ግለሰቦች ተያዙ

56
መቱ  የካቲት 6/2012 (ኢዜአ) በኢሉአባቦር ዞን ያዮ ወረዳ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ ተደርሶባቸዋል ያላቸውን ሶሰት ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳውፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ከድር አባፎጊ እንደገለፁት ግለሰቦቹ  የተያዙት ኮድ 3 -22454 አ.አ. በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ ተደርሶባቸው ነው። ግለሰቦቹ ከጋምቤላ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ አመልክተው ያዮ ወረዳ እንደደረሱ  በተደረገው ፍተሻ 40 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስታውቀዋል። ጠብመንጃዎቹን ግልሰቦቹ በተሽከርካሪው ውስጥ ደብቀው እንደተገኘባቸው ያመለከቱት ዋና ሳጂኑ  በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን  አብራርተዋል። የጋምቤላ አዲስ አበባ ዋና መንገድ በተደጋጋሚ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር የሚውሉበት በመሆኑ ቁጥጥሩ እንደሚቀጥልና ህብረተሰቡም ህገ ወጥ ድርጊትን ለመከላከልትብብሩን እንዲያጠናክር  ዋና ሳጅን ከድር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም