ሲራጅ ፈጌሳ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበርነታቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ

88
አዲስ አበባ ሰኔ 19/2010 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት ሲራጅ ፈጌሳ ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ። በምትካቸው አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ የደኢህዴን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን የንቅናቄው ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ በልጂጌ ለኢዜአ አረጋግጠዋል። አቶ ሲራጅ ደኢህዴንን ከ1980 ጀምሮ በአባልነት የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በኋላም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የንቅናቄው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ ነበር። አቶ ሲራጅ የስልጤ ዞን አሰተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ኢህአዴግ  የ1997ቱን ምርጫ ማሸነፉን ተከትሎ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ከ2001 እስከ 2010 ዓ.ም ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ባዋቀሩት አዲስ ካቢኔ ውስጥም የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም