ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የወልመል መስኖ ፕሮጀክትን አስመረቁ

56
አዲስ አበባ  ጥር (ኢዜአ) 26/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የወልመል መስኖ ፕሮጀክትን አስመረቁ። የወልመል መስኖ ፕሮጀክት በምዕራብ ባሌ ዞን በዶሎመና ወረዳ ከ400 ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም አለው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወንዝ ላይ የሚገነባ ሌላ ተጨማሪ የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። አዲስ የሚገነባው ፕሮጀክት ተጨማሪ 11 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳለው ነው የተነገረው። የወልመል ወንዝ ከባሌ ተራራ የሚመነጭ ሲሆን በምዕራብ ባሌ ዞን የዶሎመና፣ የመደወላቡና ሐረና ወረዳዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም አለው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም