በመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ሉዑክ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ነው

66
አዲስ አበባ ኢዜአ፤ጥር 20/2012 በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ቡድን በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡ በጉብኝቱ ከፈረንሳይ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች፣ የመከላከያ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ እና የኢታማዦር ሹም ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኢንባሲ እንደገለፀው ጉብኝቱ  በአየርና ባህር ሃይል  ስልጠናዎች አንዲሁም  በወታደራዊ ቁሳቁሶች  አቅርቦት ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡ ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር ለመስራት በመጋቢት ወር 2019 መፈራረማቸውና    ፓሪስም ኢትዮጵያ ለምታደረገው የባህር ሀይል ግንባታ  ኢኮኖሚያዊ እገዛ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት መግለጸ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም