ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው መስራቅ የሰላም እቅዳቸውን ይፋ አድርገዋል

86

ጥር 20/2012 (ኢዜአ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤል-ፍሊስጤም ብሎም ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ዘላቂ መፍትሄ ነው ያሉትን እቅድ ይፋ አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አዲስ ይፋ ያደረጉት እቅድ በተለይ ሁለቱንም ወገኖች “ተጠቃሚ የሚያደርግ አማራጭ” ነው ብለዋል፡፡

በአዲሱ የዶናልድ ትራምፕ የሰላም እቅድ መሰረት የፊሊስጤም መዲና ከእየሩሳሌም ከተማ በስተምስራቅ ይሆናል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በተቀመጠው የእቅዱ ፅንሰ-ሀሳብ እና ዝርዝር ፍኖት መሠረት ዙሪያ ለመደራደር መስማማቷን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለፍልስጤም ሉዓላዊ ሀገር ምስረታ እውቅና በመስጠት፤በእቅዳቸው መሰረትም አዲሱ የፊሊስጤም ዋና ከተማ ይሆናል ብለው ባሰፈሩት ምስራቅ እየሩሳሌም ላይ ሀገራቸው ኤምባሲዋን ትከፍታለች ነው ያሉት፡፡

ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ ጀምሮ ለእስራኤል ብዙ እንደለፉ የሚናገሩት ትራምፕ፤አሁን ደግሞ ለፊሊጤም ሰላም መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

እስራኤል በምትቆጣጠረው ዌስት ባንክ የምታካሂደውን የሰፈራ ፕሮግራም፤አሜሪካ እውቅና የምትሰጥ ሲሆን ነገር ግን የፍልስጤም ጉዳይ ላይ ድርድር እስከሚደረግ እስራኤል የግንባታ ስራውን ለአራት አመታት እድታቆም ፕሬዝዳንቱ ተናግራዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ እቅድ ለፍልጤም፤ግብጽ እና ዮርዳኖስ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ የሚውል 50 ቢሊዮን ዶላር ተዘጋጅቷል፡፡

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው የኦማን፤ባህሬን እና የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ አምባሳዶሮች በዋሽንግተኑ ውይይት መገኘታቸው የትራምፕ እቅድ ስኬታማ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም ቀውሱን ለመፍታት ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሙከራዎች እስራኤል ለደህንነቷ በመስጋት እንዲሁም ፍልስጤማውያን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ፍላጎት ላይ የተመሰረት በመሆኑ ሙከራዎቹ ትክክለኛውን ሚዛን አልተመቱም“ ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ትራምፕ መቼም ቢሆን እስራኤል የነበሯት “ምርጥ ጓደኛ” እንደሆኑ እና ምንም እንኳን ከዚህ በፊት በዋይት ሃውስ የእስራኤል ጥሩ ጓደኞች የነበሩ ቢሆኑም እንደ ትራምፕ ግን “ቅርብ” አይሆኑም፡፡

ምንም እንኳ ከዋሽንግተን በኩል ጥሩ ቃላት ቢኖሩም ከፊልስጤማውያን ወገን እቅዱን እንደማይቀበሉ አስቀድመው ተናግረዋል፡፡

የፍልጤሙ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አባስ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እቅድን በማጣጣል “ሴራ” ብለውታል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2017 ጀምሮ የትራምፕ አስተዳደር እስራኤል አቋም ያስቀየሩ ዋና ዋና ስምምነቶችን ቢያደርግም በፍልስጤማውያን ዘንድ በግጭቱ ውስጥ ገለልተኛ የግልግል ዳኛ ሆኖ አይታይም፡፡

ዕቅዱ ከመለቀቁ በፊት በብሪታንያ የፍልጤም ተወካይ የሆኑት ሁሳም ዞምሎት ለሮይተርስ በሰጡት መግለጫ እቅዱ “የፖለቲካ ቲያትር” እንደሆነና “ትርጉም የለሽ” ብለውታል፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሀኒ ከፍተኛ አማካሪ የትራምፕ ዕቅድ “በጽዮናዊ አገዛዝ [በእስራኤል] እና በአሜሪካ መካከል የተደረገ “ስምምነት” ብቻ እንደሆነ እና ከፍልስጤማውያን ጋር የሚያደርጉት ግንኙነት አጀንዳው አለመሆኑን በትዊተር ገፃቸው ማስራቸውን የሩሲያው አርቲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም