በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 106 መድረሱ ተረጋገጠ - ኢዜአ አማርኛ
በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር 106 መድረሱ ተረጋገጠ
85
ጥር 19/2020 በቻይና እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾች ቁጥር 106 መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን 4 ሺህ 587 የሚሆኑት ደግሞ የበሽታው ምልክት ተገኝቶባቸዋል።
እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ መሰረት በሽታው ከተገኘባቸው 4 ሺህ 587ሰዎች መካከል 4 ሺህ 535 የሚሆኑት ቻይናውያን ሲሆኑ ሌሎች 52 የሚሆኑት ደግሞ የውጫ ሀገር ዜጎች ናቸው ተብሏል፡፡
106 ሟቾች ደግሞ ግን ቻይናውያን ናቸው ተብሏል፡፡
ይህ ኖቬል ኮሮና ቫይረስ በሚል የሚያተወቀው እና በቻይናዋ ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑም በህክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል፡፡
የጤና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት ቫይረሱ የመሰራጨት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓትም 30 የሚሆኑ የቻይና ከተሞች እና ሆንግ ኮንግ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የአስቸከይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል ፡፡
ምንጭ፡-ሲ-ጂ-ቲ- ኤን