የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማና የከተማው ምክር ቤት አባላት ተጎጂዎችን ጎበኙ

64
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና የከተማው ምክር ቤት አባላት ባለፈው ቅዳሜ በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው በየካቲት 12ና በምኒሊክ ሆስፒታል እርዳታ እያገኙ ያሉ ዜጎችን  ጎበኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  አሕመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና እውቅና መስጠትን ዓላማ አድርጎ በአዲስ አበባ ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ የቦንብ ፍንዳታ መከሰቱ ይታወቃል። በዚህም በከተማዋ ባሉ ሆስፒታሎች ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊው እርዳታ እያገኙ ነው። በዛሬው እለትም በየካቲት 12ና በምኒሊክ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረጋላቸው የሚገኙ ታካሚዎችን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማና የከተማው ምክር ቤት አባላት ጉብኝት በማድረግ አጽናንተዋቸዋል። ከንቲባ ድሪባ ኩማ በጉብኝታቸው ወቅት በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸው፤ የከተማ አሰተዳደሩ ለተጎጂዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ጥቃት ያደረሱ አካላትንም ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ርብርብም ከሚመለከታቸው አካላት ጎን በመሆን የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራ አክለዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም