የደቡብ ክልል የባህል ስፖርቶች ውድደር ተጀመረ

130
ሆሳዕና ኢዜአ ጥር 18/2012 ፡- 17ኛው የደቡብ ክልል የባህል ስፖርቶች ውድደር ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተጀምረ፡፡ ለአስራ አንድ ቀናት በሚቆየው በዚሁ ውድድር ከ11 ዞኖችና ሶስት ልዩ ወረዳ የተውጣጡ በቁጥር 200 የሚጠጉ ስፖርተኞች እንደሚሳተፉ  ተገልጿል። ገና፣ ፈረስ ጉግስና ሸርጥና ገበጣ በውድድሩ ከሚካሂዱ የባህል ስፖርቶች መካከል ይገኙበታል። ውድድሩን ያስጀመሩት የክልሉ ስፖርት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብሩክ ዋኖሮ እንዳሉት የክልሉ ህዝቦች ያሏቸው ባህላዊ የስፖርት ጨዋታዎች ጠብቆ ማቆየት ይገባል። ባህላዊ የስፖርት ጨዋታዎች ህዝብን በሚያስተሳስር መልኩ ጥቅም ላይ በማዋል ክልላዊና ሀገራዊ አንድነትን ለማምጣት መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም