ቻይና በኮሮና ቫይረስ የማቾች ቁጥር  በማሻቀቡ  ብሄራዊ   የዘመን  መለወጫ በዓል  ቀኗን  አራዘመች

44
ኢዜአ፤ጥር  18/2012  በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር ወደ 81 ማሻቀቡን ተከትሎ  የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ሲባል ብሄራዊ የዘመን መለወጫ በዓሏን በሶስት ቀናት አራዘመች ፡፡ በሀገሪቱ እስካሁን ድረስ በቫይረሱ  81 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 3ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል ፡፡ ይህን ተከትሎ የቻይና አዲስ አመት ክብረ በዓል ለሶስት ቀናት የተራዘመ ሲሆን እስከ እሁድ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡ በዛሬው እለት የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ በሽታው  የተከሰተበትን የሁበይ አውራጃ ዋና ከተማ ውሃንን ጎብኝተዋል፡፡ ከሟቾች መካከል 76 የሚሆኑት የሁበይ አውራጃ ነዋሪ የነበሩ  ሲሆን ሌሎች አምስቱ ደግሞ የሌላ አካባቢዎች ናቸው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከቻይና መንግስት እና ከጤና ባለሙያዎች ጋር ስለ ወረርሽኙ ለመወያየት በቤጂንግ ተገኝተዋል ፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በውሃን ከተማ  ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር የጉዞ እገዳ ተጥሏል፡፡ (ቢቢሲ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም