አቶ ዱቤ ጅሎ የስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽር ሆነው ተሾሙ

69
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 18 ቀን 2012 ዓም  ከ10 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ዱቤ ጅሎ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል። አቶ ዱቤ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል። ቀደም ብሎም ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ የአትሌቶች ተወካይ በመሆን ከዚያም በፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባል ሆነው ሰርተዋል። አቶ ዱቤ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን በማገልገል ላይም ናቸው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስፖርት ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ዱቤ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም