በወላይታ የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከሰተ

87
ሶዶ ጥር 17 /2012 (ኢዜአ)  በወላይታ ዞን የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ። የመምሪያው ሃላፊ አቶ አሞና ቶልካ እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ  በዞኑ በሚገኙ ዱጉና ፋንጎ ወረዳዎች መታየት ጀምሯል ። በተለይ ደግሞ  ድምቱ፥ብላቴ ኤታና ወርቅቻ ደንዶ በሚባሉ ቀበሌያት መንጋው በስፋት መከሰቱን ተናግረዋል ። የአንበጣው መሬት ላይ እንዳያርፍና ጉዳት እንዳያደርስ የተለያዩ ባህላዊ ዜዴዎች በመጠቀም ህብረተሰቡ እያባረረው መሆኑን ገልፀዋል ። የአንበጣው መንጋ እስከ አሁን ድረስ ያደረሰው ጉዳት የለም ያሉት መምሪያ ሃላፊው ህብረተሰቡ በተደራጀ መልኩ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልእክት አስተላልፈዋል ።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም