የ" ደራሮ " በዓል በዲላ ከተማ እየተከበረ ነው

78
ጥር 16/2012 (ኢዜአ) የጌዴኦ ብሔር ዘመን መለወጫ የ”ደራሮ “ በዓል በዲላ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው። በበዓሉ ስነስርዓት የደቡብ ክልልና የፌደራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ ብሔርና  ብሔረሰቦች ተወካዮች ተገኝተዋል። በዓሉን  ምክንያት በማድረግም  አዳሪ ትምህርት ቤት ለመገንባት መሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የ" ደራሮ " በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር መሰንበቱንና ዛሬ ደግሞ  የማጠቃለያው  ስነስርዓት  እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም