ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኦሎምፒክ ውድድር ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

55
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 15/2012  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እ.አ.አ በ2020 በቶኪዮ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ዝግጅት ለማስተባበር ከተቋቋመው ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ማብሪሪያ መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጸህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ኮሚቴው ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ለውድድር መላክ ብቻ ሳይሆን፣ በድል እንዲመለሱም የማገዝና ድጋፍ የማድረግ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2020 በሚካሄደው የጃፓን ቶኪዮ 32ኛው የኦሎምፒክ ውድድር በአትሌቲክስ፣ በቦክስ፣ በእግር ኳስ፣ በብስክሌት፣ በውሃ ዋና፣ በካራቴ፣ በወርልድ ቴኳንዶና ዒላማ ተኩስ ስፖርቶች ለመሳተፍ እቅድ ይዛለች። በተደረጉ ግምገማዎች ቅርጫት ኳስና እጅ ኳስ ውድድሮች ከሌሎቹ ከታቀዱት 8 ስፖርቶች በተጨማሪ በእቅድ ውስጥ ለማካተት ሀሳብ እንዳለ ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ስፖርቶች በቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድር አገራቸውን ወክለው መሳተፍ በሚያስችላቸው የማጣሪያ ውድድሮች ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም