የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ - ኢዜአ አማርኛ
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ
63
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን / ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን የንቅናቄው ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ። ኮሚቴው በጠራው አስቸኳይ ስብሰባው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ወይዘሮ ሙፈሪያትን የንቅናቄው ሊቀ-መንበር አድርጎ የመረጠው የቀድሞው የንቅናቄው ሊቀ-መንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ዛሬ ኃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው። ሥራ አስፈፃሚው የንቅናቄው ምክትል ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ ሲራጅ ፈጌሳን በኃላፊነታቸው አንዲቀጥሉ ወስኗል። አቶ ሽፈራው አሁን ያለውን የለውጥ ሂደት እንደሚደግፉና በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደሚቀጥሉ መናገራቸውም ተመልክቷል።