ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 3 ሚኒስትሮችን ሾሙ

78
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 13/2012  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሶስት አዳዲስ የሚኒስትርነት ሹመቶችን ሰጡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት አዳዲስ የሚኒስትርነት ቦታዎች ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ የትምህርት ሚኒስትር፣ አቶ መላኩ አለበል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር እንዲሁም  ዶክተር አብርሃም በላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ሚኒስትሮቹ ከጥር 6 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መሾማቸውን  ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም