አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ

87
የደኢህዴን ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ፡፡ የደኢህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ሽፈራው ከሊቀመንበርነታቸው ለመልቀቅ ምክንያት ናቸው ያሏቸውን  ነጥቦችም ሲገልጹ እንዳሉት፡-
  • መቀመጫቸው አዲስ አበባ በመሆኑ ክልሉን በቅርበት መደገፍ አለመቻላቸው
  • በአገሪቱ እየታየ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ በአዲስ መንፍስ እንዲቀጥል የህዝቡ ጥያቄ በመሆኑናለዚህ ዕድል ለመስጠት
  • በክልሉ የተፈጠሩ ግጭቶች ከአመራር ክፍተት የመነጩ በመሆናቸው የመፍትሔው አካል ለመሆንነው ብለዋል።
የደኢህዴን ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኃይለመሪያም ደሳለኝ ከድርጂቱ ሊቀመንበርትን ከለቀቁ ብኋላ   አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የደኢህዴን ሊቀመንበር ሆነው  መመረጣቸው ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም