አዲስ በተከሰተ ቫይረስ ምክንያት ወደ ውሃን ከተማ ጉዞ እንዳይደረግ ቻይና አስጠነቀቀች

59

ኢዜአ፤ ጥር/ 20212  በቻይና ውሃን ከተማ በተከሰተ አዲስ ቫይረስ ( 2019-nCoV) ምክንያት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ወደ ከተማዋ የመግባትም ሆነ የመውጣት ጉዞ እንዳይደረግ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል፡፡

በውሃን ግዛት እስካሁን በተደረገው ምርመራ ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ 440 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ህዝብ በብዛት ወደ ሚሰባሰብባቸው አካባቢዎች መሄድ እንደሌለባቸውም ባለስልጣናቱ መክረዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ በበርካታ የቻይና ግዛቶች ተሰራጭቷል።

ከዚህ በተጨማሪም ቫይረሱ አሁን ላይ ወደ አሜሪካ፣ ታይላንድና ደቡብ ኮሪያ እንደተዛመተ መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡

ወደ ፊትም ቫይረሱ ብዙ ግዛቶችን ሊያዳርስ እንደሚችል አመላካች ነው ሲሉ የቻይና ጤና ሚኒስትር ሊ ቢን ተናግረዋል።

የቫይረሱ ስርጭት በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመሆኑ ሀገሪቱ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት ባለስልጣናቱ አሳስበዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም