የቤንሻንጎል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀመራል

64
አሶሳ ጥር 11/2012  (ኢዜአ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤውን ከጥር 12 እስከ 13/2012 እንደሚያካሒድ አስታወቀ። የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተክቶ ታደሰ ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት ምክር ቤቱ አምስተኛ የስራ ዘመን አስረኛ መደበኛ ጎባኤውን ከጥር 12 እስከ 13/2012 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ያካሄዳል። የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት፣ የርዕሰ-መስተዳደር ጽሕፈት ቤት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት ቢሮ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀምን መመልክት የጎባኤው ዋናኛ አጀንዳ መሆናቸውም ተገልጿል። ምክር ቤቱ በሌሎች ወቅታዊና ክልላዊ እንዲሁም ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይም እንደሚወያይ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም