የዞኑ ዓመታዎ የባህል ስፖርት ውድድር በቦነያ ቦሴና በሲቡ ሲሬ ወረዳዎች የበላይነት ተጠናቀቀ

80
ነቀምቴ ጥር 11 / 2012  በምስራቅ ወለጋ ዞን ዘጠኝ ወረዳዎች መካከል የተካሄደው ዓመታዎ የባህል ስፖርት ውድድር በቦነያ ቦሴና በሲቡ ሲሬ  ወረዳ ዎች የበላይነት ተጠናቀቀ። ውድድሩ በሲሬ ከተማ ላለፉት አምስት ቀናት በስምንት የባህል ስፖርት ዓይነቶች ተካሂዷል ። ቦነያ ቦሴ በቡብ፣ በገበጣ ናለ 12 እና 18 ጉድጓዶች በሁለቱም ፆታዎች  ሦስት ዋንጫዎችን አግኝቷል። ሲቡ ሲሬ ደግሞ በወንዶች የገና ጨዋታና በትግል በሁለቱም ፆታዎች በማሸነፍ የሶስት ዋንጫዎች ባለቤት ሆኗል። የጎቡ ፈዮ በኮርቦ በሁለቱም ፆታዎች በማሸነፍ ሁለት ዋንጫዎች ሲወስድ፣ጉቶ ጊዳ የቀስት ውድድርን  አሸንፏል። ሳስጋ ደግሞ የፀባይ ዋንጫ ተሸልሟል።በውድድሩ ዞኑን በመወከል በዚህ ዓመት በፍቼ ከተማ በሚካሄደው የኦሮሚያ ክልል የባህል ስፖርት ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉት 16 ተወዳዳሪዎች ተመርጠዋል። የዞኑ የስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ዮሐንስ ብየና ለአሸናፊ ወረዳዎች የተዘጋጁላቸውን ዋንጫዎች ከሰጡ በኋላ ባደረጉት ንግግር ዞኑን  የሚወክሉት ስፖርተኞች  ውድድሮቻቸውን በብቃትና በመልካም ሥነ ምግባር እንዲያከናወኑ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም