ወላይታ ዲቻ ጅማ አባ ጅፋርን ሁለት ለአንድ አሸነፈ

56
ጅማ፤ ጥር 10/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዘጠነኛው ሳምንት ጨዋታ ወላይታ ዲቻ ጅማ አባ ጅፋርን ሁለት ለአንድ አሸነፈ፡፡ ውጤቱ ወላይታ ዲቻ በዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ድል አስመዝግቧል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ሁለቱም ቡድኖች በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ተግባራዊ አድርገዋል። ባለሜዳዎቹ ጅማ አባጅፋሮች በቅድሚያ ግብ በማስቆጠር ከዕረፍት በፊት የነበረው ክፍለ ጊዜ ተጠናቀቀ። በሁለተኛው ግማሽ ተጠናክረው ወደ ሜዳ የገቡት ወላይታ ዲቻ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር  የውድድሩ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ወላይታ ዲቻ ማሸነፉን ተከትሎ ከወራጅ ቀጠና ወጥተው 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ጅማ አባጅፋር በነበረበት 11ኛ ደረጃ  የቆየ ሲሆን፣የሰበሰበው ነጥብ 10 ነጥብ ነው፡፡ ሊጉን መቀሌ 70 እንደርታ በ19 ነጥብ በመምራት ላይ ነው። ሦስቱ የከተማ ክለቦች ወልቂጤ በ16ኛ፣ሐዲያ ሆሳዕና 15ኛ ና አዳማ ከነማ 14ኛ ደረጃዎችን በመያዝ በወራጅ ቀጠና ውስጥ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም