የጥምቀት በአል ለሁሉም ማህበረሰብ ፍላጎት የሚሆኑ አዳዲስ ዲዛይኖች ያላቸው የባህል አልባሳት የቀረበበት ነው…አስተያየት ሰጪዎች

314
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 10/2012 የጥምቀት ክበረ በአልን አስመልክቶ የባህላዊ አልባሳት ለሁሉም ማህበረሰብ ፍላጎት የሚሆኑ አዳዲስ ዲዛይኖችን የተሰሩ የባህል አልባሳት ለገበያ መቅረባቸውን  አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ  ነጋዴዎችና ሸማቾች ተናገሩ፡፡ ለጥምቀት በአል በአዳዲስ ዲዛይን የተሰሩ  የባህል አልባሳትን  ለገበያ ማቅረባቸውን  የባህላዊ አልባሳት ነጋዴዎች ተናገሩ፡፡ የኢዜአ ሪፖርትር የጥምቀት በአልን አስመልክቶ የባህላዊ አልባሳት ገበያ ምን እንደሚመስል  በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ነጋዴዎችንና ሸማቹን ማህበረሰብ አስተያየት ጠይቋል፡፡ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ በአደባባይ ከሚከበሩ ክበረ በአለት መካከልና የሀገር ባህላዊ አልባሳት በስፋት ከሚለበሱባቸው በአላት መካከል   ጥምቀት  ተጠቃሽ ነው፡፡ በአዲስ አበባ የሀገር ባህል አልባሳት በስፋት ለገበያ ከሚቀርብባቸው ቦታዎች መካከል ሽሮ ሜዳ አካባቢ ባደረገው ቆይታም የተለያዩ ማህብረተቦች ባህላዊ ልብሶችን በሁሉም እድሜ ደረጃ ባህላዊ ልባሶት በአዳዲስ ዲዛይኖች ተዘጋጅተው ለገበያ መቅረባቸውን ተመልክቷል፡፡ ሽሮሜዳ አካባቢ በባህላዊ  አልባሳት ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት ወይዘሮ እጹብድንቅ ረጋሳ  ጥምቀት በአል ለዘርፉ ነጋዴዎች ስላለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለኢዜአ እንደገለጹት ከሌላው ጊዜ በተለየ ሀገራዊ የባህል አልባሳት የሚፈለግበትና የሚለበስበት  ከሌላው ጊዜ የተሻለ ገበያ የሚገኝበት መሆኑን ታሳቢ ያደረገ የአቅርቦት ዝግጅት አድርገዋል፡፡ ለዚህም ወጣቱን የህበረተሰብ ክፍል ያማከለ  አዳዲስ  ዲዛይኖችን በመጨመር በርካታ የሴቶችና የወንዶች  አልባሳትን አዘጋጅተው ለገበያ ማቅረባቸውን ነው የጠቀሱት፡፡ ለወጣቱ ከ350 ብር ዋጋ ያላቸው አልባስተን ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን አልባሳት  መዘጋጀታቸውን  የሚገልጹት ወይዘሮ እጹብድንቅ ፤ተጠቃሚው ህብረተሰብም  እየሸመት በመሆኑ የተሸለ ገበያ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ አሁንም እየተዘጋጁ ያሉ የባህል አልባሳት ከባአል ቀናት በተጨማሪ በማንኛውም ዝግጅት ወቅት ሊለበሱ  የሚችሉ የባህል አልባሳትን አዘጋጅተው ማቅረባቸውን የጠቀሱት ነጓዴዋ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን የራሳቸውን  ባህላዊ አልባሳትን  እንዲያውቁና በራሳቸው ባህል እንዲኮሩ  የማሳየት ስራ ይጠበቅባቸዋል በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ለጥምቀት በአል አዳዲስ ዲዛይን ያላቸውን የባህላዊ አልባሳትን አዘጋጅተው ለገበያ መቅረባቸውን የሚገልጹት ደግሞ የባህላዊ አልባሳት ነጋዴ  አቶ መሀመድ ከሳ ናቸው፡፡ ሀገራዊ የባህል አልባሳትን ዲዛይን ፎቶ አንስቶ ወደቻይና በመውሰድ በዝቅትኛ ቁሳቁስ ተመሳስለው ተሰርተው በሚመጡ ዲዛይኖች የሚሰሩ ልብሶች  በሀገር በቀሉ ልብስ ላይ ተጽኖ እያሳደረ መሆኑን አቶ መሀመድ ተናግረዋል፡፡ ከበአሉ ጋር ተያይዞም ተጠቃሚው ማህበረሰብ እንደአቅሙና ፍላጎቶ እንዲያገኝ ለማድረግ ከ500 ብር እስከ 2000 ብር ድረስ ዋጋ ለቸው ባህላዉ አልባሳት አዘጋጅተው ለገበያ መቅረባቸውን ተናገረዋል፡፡ ለጥምቀት በአል የሀገር ባህል ልብስ ሲገዙ አግኝተን ያነጋገርናቸው ወይዘሮ ሸዋዬ ሃይለመስቀል በበኩላቸው ለበአሉ የሚያማር በአዳዲስ ዲዛይኖች የተሰሩ አልባሳት በስፋት ማግኘታቸውንና ሸማቹ እንደአቅሙ እንዲገዛም ከ500 ብር እስከ 10ሺህ ብር ዋጋ ያላቸው ልብሶች በባዛሩ ላይ ቀርቦ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ለበአሉም  በስፋት የሀጋር ባህል ልብስ ተዘጋጅቶ መቅረቡ ህብረተሰቡ ወደራሱ  ባህል እንዲሳብ ያደርገዋል ያሉት ወይዘሮ ሸዋዬ፤ በሁለት ሺህ ብር ዋጋ  ከባአሉ ባለፈ ለሌሎች ዝግጅት የሚለበስ የባህላ ልብስ መግዛታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም