ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍንዳታው የሞቱ ዜጎች ቤተሰቦችን አጽናኑ

70
አዲስ አበባ ሰኔ  18/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በደረሰ የቦምብ አደጋ ህይወታቸው ያለፈውን የዮሴፍ አያሌው እና የቡሳ ጋዲሳን ቤተሰቦች አጽናኑ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደጋው የሞቱ ሰልፈኞች ቤተሰቦችን በስልክ ደውለው ማጽናናታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የ28 ዓመት ወጣት የሆነው ዮሴፍ አያሌው የወላይታ ሶዶ ተወላጅ ሲሆን የ25 ዓመቱ ጉሳ ጋዲሳ ደግሞ የወለጋ ጊምቢ ተወላጅ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞቱት ሰዎች ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸውና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተው፤ መንግስትና የኢትዮጵያ ህዝብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና ዕውቅና ለመስጠት ከትናንት በስቲያ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ መገኘቱ የሚታወስ ነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም