በአፈ-ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም የተመራ ቡድን ተጎጂዎችን እየጎበኘ ነው

92
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂምና የምክር ቤቱ ሰራተኞች በመስቀል አደባባይ በደረሰው ፍንዳታ የተጎዱ ዜጎችን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተገኝተው እየጎበኙ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላስመዘገቡት ለውጥ ድጋፍና ዕውቅና ለመስጠት ከትናንት በስቲያ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ የቦምብ አደጋ መከሰቱ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ150 በላይ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። የአደጋው ሰለባዎች በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመገኘት ተጎጂዎችን ጎብኝተዋል። ሌሎች አካላትም በተከታታይ ተጎጂዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም