ለልምምድ ወደ ናሳ ያቀናው የ17 ዓመት አሜሪካዊ ወጣት በሶስተኛ ቀኑ አዲስ ፕላኔት አገኘ

178
ጥር 7/2012 (ኢዜአ) ናሳ ውስጥ ለልምምድ የገባው የ17 አመት አሜሪካዊ ታዳጊ  ወልፍ ኩኬር ከምድር በ1 ሺህ 300 የብርሃን አመታት የምትርቅ አዲስ ፕላኔት አግኝቷል። ወጣቱ  ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ ለሁለት ወራት  በአሜሪካ   የሕዋ ምርምር ማዕከል (ናሳ) ተመድቦ የልምምድ ተግባሩን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ታዳጊው ከአንድ ትልቅ ሳተላይት ምስሎችን እየተከታተለ በነበረበት ወቅት ነው አዲስ ነገር የተመለከተው። "በሰዓቱ ሁለት ኮከቦችን የምትዞር አንዲት ፕላኔት እየፈለግኩ በነበርኩበት ወቅት  የክዋክብቱን ደማቅነት የሚቀይር የፕላኔት ጥላ የሚመስል ነገር ተመለከትኩ" ብሏል ። ወደ ማእከሉ በገባ በሦስተኛው ቀን ወጣት ወልፍ የተመለከተው እና የሁለቱን ክዋክብት ብሩህነት የሚቀይረው ነገር ላይ በተሠራው ትንተና የታየው ጥላ ከምድራችን በርካታ የብርሃን ዓመታት የሚርቅ ፕላኔት መሆኑ በዘርፉ ባለሞያዎች ተረጋግጧል። አዲሱ ፕላኔት ከመሬት 6.9 እጥፍ ገደማ የሚበልጥ ግዝፈት ያለው ሲሆን የተገኘችው ፕላኔት ቲ ኦ አይ 1338 ቢ የሚል ስያሜ አግኝታለች። ምንጭ።-በቢሲ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም