ካሜሩን በቀጣዩ ወር የሚካሄደውን ምርጫ ሊያውኩ ያሰቡ አካላትን አስጠነቀቀች

58

ኢዜአ፤ ጥር 6/2012 የካሜሩን መንግስት እ.ኤ.አ. የካቲት 9/2020 የሚካሄደውን ምርጫ ለማደናቀፍ አቅደው የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግ  አስታወቀ፡፡

 ቢቢሲ እንደዘገበው የካሜሩን ተገንጣዮች በሁለት የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንዳያውኩ ስጋት ማሳደራቸውንም በዘገባው ተመልክቷል።

እንደ ዘገባው የካሜሩን መንግሥት እንግሊዝኛ ተናጋሪ (አንግሎፎን) ዜጎች በሚኖሩበት ክልል አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደህንነት ሀይል አሰማርቷል።

በቅርቡ 800 ወታደራዊ የፖሊስ መኮንኖች ከመዲናዋ ያውንዴ በስተሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ ዋና አቅጣጫ የሚገኙ ሁለት ከተሞችን እንዲጠብቁ መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡

የተገንጣይ ተዋጊዎች በእንግሊዝኛ ተናጋሪ ክልሎች አካባቢ ምርጫ እንዳይካሄድ የሚያውኩ ከሆነ ከምርጫው አንድ ሳምንት በፊት  አገልግሎቶች ላይ እገዳ እንደሚያደርግ መንግስት ይፋ አድርጓል።

የሀገሪቱ ዜጎች በየካቲት ወር በሚያደርጉት ምርጫ የምክር ቤት እና የከተማ አስተዳደር ተወካዮቻቸውን እንደሚመርጡ ዘገባው አመልክቷል።

የድንበሮች አስተዳደር ሚኒስትር ፖል አታንጋ ንጂ የደህንነት ኤጀንሲዎች ምርጫውን በሚያጭበረብሩ ሰዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንሚያደርጉ አስጠንቅቀዋል።

የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ክልሎችን የሚቆጣጠሩ ፖሊሶች ከዚህ በፊት በወሰዱት የጭካኔ እርምጃ ተከሰው እንደነበር ቢቢሲ አስታውሷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም