ድቻ በስሁል ሽሬ ተሸነፈ

57
ኢዜአ ፤ጥር 3/2012 በወላይታ ሶዶ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው ስምንኛው ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ስሁል ሽሬን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ ሁለት ለባዶ ተሸነፈ። የሲሁል ሽሬ የማሸነፍያ ግቦችን ያስቀጠረው በ20ኛው ደቂቃ ረመዳን ዩሱፍ እና በ92ኛው ደቂቃ ደግሞ በሀብታሙ ሸዋለም በኩል በፍጹም ቅጣት ምት ነው። በጨዋታው ተሽሎ የቀረበው ሲሁል ሽሬ በተጋጣሚው ደጋፊዎች ሙገሳ ተችሮታል ። በአንጻሩ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች በቡድናቸውና አመራሩ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በስታዲየሙ ውስጥ ባሰሙት ድምጽ ገልጸዋል። አሸናፊው ሲሁል ሽሬ የደረጃ ለውጥ ሲያደርግ ተሸናፊው በወራጅ ቀጠና ሊቀጥል ተገዷል ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም