ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚደንት ራማፎሳ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ግንኙነት ላይ ውይይት አካሄዱ

84
ኢዜአ ፤ጥር 3/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ልዑካን ቡድናቸው ከፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር በሁለቱ ሀገራት የጋራ ግንኙነት ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱ ወቅት ከተነሱት ቁልፍ ጉዳዮች ውስጥ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን ግንኙነት ወደ ስትራተጂያዊ አጋርነት ከፍ ማድረግ፣ በኢትዮጵያ በመጠናከር ላይ ባሉ ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንት ማካሄድ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባነሷቸው ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ቅኝት ማካሄድ ይገኙበታል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚከተሉትን ስምምነቶች አፈራርመዋል፦ 1. ዲፕሎማሲያዊ እና ኦፊሴላዊ ፓስፖርት ለያዙ የሚሆን የቪዛ ፈቃድ፣ 2. በቱሪዝም መስክ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት፣ 3. በጤናው ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት። እንደሚገኙበት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም