ታሪክ ትምህርት ቤት እንጂ እስር ቤት መሆን የለበትም - ኤምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ

98

ኢዜአ ታህሳስ 30/2012 ታሪክ ትምህርት ቤት እንጂ እስር ቤት መሆን የለበትም ሲሉ ኤምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ገለጹ።

ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በየወሩ መጨረሻ በሚያደርገው የውይይት መድረክ ላይ 'የኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ፣ ዕድገቱና ተግዳሮቱ' በሚል ፅሁፍ አቅርበዋል።

በፅሁፋቸው የኢትዮጵያ ታሪክ አፃፃፍ፣ ዕድገት፣ ድክመትና ጠንካራ ጎኖችንም ዳሰዋል።

በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ግቢ እየተደረገ ባለው ውይይት ጽሁፍ ያቀረቡት የኤምሬትስ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ የወደፊት አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጡም 'ታሪክ ትምህርት ቤት እንጂ እስር ቤት መሆን የለበትም' ብለዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ መልካምም፣ መልካም ያልሆኑ ክስተቶችም ተፈጥረዋል ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ "በታሪክ ላይ በትናንትናው ድርጊት ማላዘን አይጠቅምም፤ ከዚያ ይልቅ የተሻለ ነገር ለመፍጠር ወደፊት መራመድ ነው አዋጭ" ብለዋል።

"በኢትዮጵያ የታሪክ መነታረክ ምርጫው አብሮ መኖር ወይም አብሮ መጥፋት ነውም" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም