የመንግስታቱ ድርጅት ሽብርተኝነት በሳህል ቀጠና አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ነው አለ

64

ታህሳስ 30/2012   በሳህል ቀጣና ሽብርተኞች ሲቪል ሰዎችን እና ወታደራዊ ቦታዎችን የጥቃታቸው ኢላማ እያደረጉ መምጣታቸውን የአካባቢው የመንግስታቱ ድርጅት ልዑክን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

የመንግስታቱ ድርጅት ልዑኩ መሐመድ ኢብን ቻምባስ ይህን የተናገሩት የፀጥታው ም / ቤት ባካሄደው ውይይት ላይ እንደሆነ መረጃው ጠቁሟል።

እ.ኤ.አ ከ2016 ወዲህ በማሊ ፣ በቡርኪና ፋሶ እና በኒጀር  በታጣቂዎች እየደረሰ ያለው ጥቃት በአምስት እጥፍ እየጨመረ እንደመጣ ልዑኩ አክለዋል።

እ.ኤ.አ. 2019 በደረሰ ጥቃት ከ4ሺ በላይ ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት ከነበረው 770 ጋር ስነፃፀር ከፍተኛ እንደሆነ ሪፖርቱ ያሳያል ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

የተባበሩት መንግስታት የቅርብ ጊዜ ጥቃቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ከነዛ ወስጥ በማዕከላዊ ማሊ በመንገድ ላይ በተጠመደ ቦንብ አምስት ወታደሮች የሞቱ ሲሆን በተመሳሳይ በቡርኪና ፋሶ በደረሰ አደጋ 14 ሰዎች ህይወት ቀጥፏል፤እ.ኤ.አ 2019 ታህሳስ ወር በሰሜናዊ ቡርኪና ፋሶ በሶኒ በሚገኝ ወታደራዊ ጣቢያ ላይ በደረስ ጥቃት 35 ሰላማዊ ሰዎች እንደሞቱ የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንደሚያሳይ ቢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም