ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ የመስቀል አደባባዩን የቦንብ ፍንዳታ አወገዙ

109
አዲስ አበባ ሰኔ17/2010 የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ስራ ዕውቅና ለመስጠት በመስቀል አደባባይ በተጠራ ሰልፍ ላይ የተከሰተውን የቦንብ ፍንዳታ አወገዙ። ፕሬዝዳንቱ በተፈጠረው አደጋ ማዘናቸውን ገልጸው፤ ይህን መሰሉን እኩይ ተግባር ለመዋጋት እርሳቸውም ሆነ አገራቸው ኬኒያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን መሆናቸውን አረጋግጠዋል። የኬኒያና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወዳጅነት ጊዜና ሁኔታዎች የማይገድቡት መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንት ኡሁሩ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ወደፊትም በክፉም በደጉም አብረው እንደሚሆኑ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለህዝቦች አንድነት መስራት፣ አገር የማረጋጋት ብሎም ወደ ብልጽግና የመውሰዱን ተግባርና ተነሳሽነት አሁንም ማጠናከር ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም