የኦሮሞ ዴሞኪራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የኦሮሞ ዴሞኪራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ
61
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 ለውጥና መደመርን በሚያወድሰው በመስቀል አዳባባዩ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች የኦሮሞ ህዝብ ዴሞኪራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ። ድርጅቱ በይፋዊ ድረ-ገጹ እንዳስታወቀው የዚህን ዓይነቱን እኩይ ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦችን በማውገዝ ለተጎጂዎቹና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ተመኝቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና እውቅና መስጠትን ዓላማ አድርጎ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተደረገው ሰልፈ ላይ ፍንዳታ ደርሶ ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።