ኢትዮጵያዊው ወጣት በአንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የምትችል ተሽከርካሪ ሰራ

57

ኢዜአ፤ ታህሳስ 21/2012 በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ተወልዶ ያደገው የ11ኛ ክፍል ተማሪው አጃዬ ማጆር      በአንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 40 ኪሎሜትር የምትጓዝ ተሽከርካሪ ሰርቷል።

ወጣቱ የወዳደቀ ብራታ-ብረትን በመጠቀም ነው ተሸከርካሪዋን ያመረታት፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባደረገለት ድጋፍ የተሰራችው ተሸከርካሪዋ የባለ ሁለት እግር ተሸከርካሪ ሞተርን በመጠቀም የተሰራች ሲሆን መሄድ እንድትችል (reverse gear) አድርጎ እንዳሻሻላትም ተነግሯል።

ተሸከርካሪዋ አራት ኩንታል ክብደት ያላት ሲሆን እስከ 4 ሰዎች የመጫን አቅም አላት፡፡ አጃዬ ማጆር ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ መኪና መስራቱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሚኒስቴሩ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግለት ሲሆን በመኪና እቃዎች ማምረትና መገጣጠም ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች አብረውት እንዲሰሩም ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም