ጅቡቲና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ አወገዙ

87
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 ጅቡቲና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ አወገዙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና እውቅና መስጠትን ዓላማ ያደረገ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰልፉ ላይ በመገኘት ለታዳሚዎች ከጥቂት ሰዓታት በፊት መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ፍንዳታ መድረሱ ይታወቃል። የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በመስቀል አደባባይ የደረሰውን ፍንዳታ እንደሚያወግዙ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል። ፍንዳታው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ መሐመድ ስልጣን ከያዙ ጀምሮ የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠንከርና ለማበልጸግ እየወሰዷቸው ያሉ ጠንካራ ማሻሻያዎችን የሚቃወሙ የተወሰኑ ሃይሎች ያደረጉት ተግባር ነው ብለዋል። በተመሳሳይ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ አውግዟል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላመጧቸው ስኬቶች ዕውቅና ለመስጠትና አጋርነትን ለመግለፅ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተደረገ የድጋፍ ስልፍ ላይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ አውግዟል። የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የተጎዱት በፍጥነት እንዲያገግሙም ተመኝቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም