የመዲናዋ ክረምት በጎ ፍቃደኞች የማጠናከሪያ ትምህርት ሊጠናከር ይገባል- ርዕስ መምህራን

85
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 በክረምት የበጎ ፍቃደኞች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ርዕሰ መምህራን ተናገሩ ። የማጠናከሪያ ትምህርቱ ተማሪዎችን አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ ከማድረግ ባለፈ ለቀጣይ  ዓመት ትምህርት ዘመን ውጤታማ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል ብለዋል። አስተያየታቸውን  ከሰጡን መካከልም  በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ  የብስራት አንደኛ ደረጃና የእፎይታ ሁለተኛ ደረጃ  እንዲሁም  በጉለሌ  የሐምሌ 67 የመጀመሪያ ደረጃ  ትምህር ቤት  ርዕስ መምህራን እንደሚሉት ለመጪው የትምህርት ዘመን ተማሪዎች የተለያዩ የትምህርት ቅድመ ዝግጅቶች ያስፈልጓቸዋል ። ይህን በማድረግ ወጣት ተማሪዎች የእረፍት ጊዚያቸውን  በአልባሌ ቦታዎች  እንዳያሳልፉ ከማድረግ ባሻገር ተማሪዎች ለቀጣይ  ዓመት በትምህርታቸው ብቁና ውጤታማ  እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ሲሉም ገልጸዋል። በመሆኑም ትምህርት ቤቶችም በበጎ ፍቃደኝነት ለሚመጡ ወጣት አገልጋዮች  የመማሪያ ክፍሎችን በማዘጋጀትና  የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት በኩል  ቅድመ ዝግጅታቸውን  ማጠናቀቃቸውንም ይናገራሉ። አቶ በኃይሉ ሽፈራው በኮልፌ የእፎይታ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ርዕሰ መምህር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተማሪዎች ትምህርታቸው ወደ ቀጣይ ክፍል ለተዘዋወሩ ተማሪዎች የትምህርት አገልገሎትን ሲሰጡ ነበር፤ በዘንድሮ ዓመት  ከወረዳው መስተዳደር ጋር  ተነጋግረን ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት ተነጋግረናል አቶ ጥላዬ ዘውዴ በኮልፌ ቀራኒዮ  ክፍለ ከተማ  የብስራት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  ርዕሰ መምህር ይህ የክረምት ስራ በተለይ ዩኒቨርስቲ ላይ ለሚቆዩ ልጆች በሚቀጥለው ጊዚያቸው ሌሎችን ማገልገል ለሌሎች ሰዎች ያላቸውን ነገር ማካፈልን የሚለምዱበት ትሬንድ ስለሆነ ይበረታታል፤ ወይዘሮ  አበባዬ ደምሴ  የሐምሌ 67 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት እኛ ትምህርት ቤት ላይ በበጎ ፍቃድ ወጣቶች የሚሰሩ በርካታ ሰራዎች አሉ፤ በበጎ ፍቃድኝነት የሚሰጡ ድጋፋቸው አገራዊ  ፋይዳው  በጣም ከፍተኛ ነው። አገሪቷ  ካላት የህዝብ ብዛት ውስጥ  አብዛኛውን ቁጥር  የያዘው ወጣቱ ክፍል መሆኑን የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ የሚረጋገጠው ደግሞ በእነዚህ ወጣቶች ተሳትፎ መሆኑም በተደጋጋሚ  ይወሳል ። ለዚህም ምስክር የሚሆኑ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች ግምባር ቀደም ተሳትፎ በማድረግ ዘርፈ ብዙ ለውጦች እንዲመዘገቡ እያደረጉ ይገኛሉ። በክረምት ወቅትም በበጎ ፍቃደኞች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎችን አልባሌ ቦታ ከመዋል የሚታደጋቸው በመሆኑ በዚህ ዓመትም  በተነቃቃ መልኩ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል ። ትምሀረት ቤቶችና የሚመለከታቸው አካላትም በትኩረት መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም