የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ በመስቀል አደባባይ የተከሰተውን ፍንዳታ አወገዙ

96
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 በመስቀል አደባባይ በተደረገው ሰልፍ ላይ የእጅ ቦምብ ይዘው ጥቃት ያደረሱ ግለሰቦችን ለፖሊስ ማስረከባቸውን የዐይን እማኞች ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ  ወደ ኃላፊነት ከመጡ በኋላ ላመጧቸው ለውጦች ድጋፍና እውቅና መስጠትን ዓላማ ያደረገው ሰልፍ ዛሬ መካሄዱ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰልፉ ላይ በመገኘት ለሰልፉ ታዳሚዎች መልእክት ካስተላለፉ ከደቂቃዎች በኋላም የቦምብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። ፍንዳታ የተከሰተበት አካባቢ ከነበሩ የዐይን እማኞች መካከል ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተመለከተውን ነገር የገለጸ ግለሰብ እንደሚለው ከሆነ እነርሱ ከነበሩበት አካባቢ በትንሽ የእጅ ቦርሳ በምትመስል ነገር የእጅ ቦንብ አውጥተው ሲወረውሩ ተመልክተዋል። ግለሰቦቹ የመጀመሪያውን እንደ ወረወሩ አካባቢው ከነበሩ ሰዎች ጋር ተረባርበው እንደያዙዋቸውና ህዝብ በስሜት እንዳይጎዳቸው ለመረጃ እንደሚያስፈልጉ በማግባባት ሁለት ግለሰቦችን አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ይዘው ለፖሊሲ እንዳስረከቡ ነው የተናገሩት። ከነሱም መካከል ቦንብ አውጥታ የወረወረችውን ሴት ይዘው ለፖሊስ እንዳስረከቡ ነው ከዐይን እማኞቹ አንዱ የሆኑት ገረመው ጌታነህ የተናገሩት። በጊዜው ሀዘን እንደተሰማቸውና መሆን የማይገባው ድርጊት መፈፀሙን ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም