በሰዎች የመነገድናበሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ላይ ተመከረ

117

ኢዜአ ታህሳስ 15 / 2012 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ላይ የባለድርሻ አካላት ውይይት አካሄዷል።

አዋጁ የሞት ቅጣት ውሳኔን እንዲያነሳና ለግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጥም ተጠየቋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የሴቶች፣ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ላይ ዛሬ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክረዋል።

በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከዚህ በፊት የወጣውን አዋጅ ቁጥር 909/2007 ሙሉ ለሙሉ የሚተካ መሆኑም ተመልክቷል።

በአዲሱ አዋጅ ላይ ማብራርያ የሰጡት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክተር  በላይሁን ይርጋ እንደተናገሩት፤ አዋጅ ቁጥር 909/2007ን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት ያስፈለገው በሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው።

አዋጁን በማርቀቅ ሂደትም በርካታ የዘርፉን የሕግ ምሁራን ከማማከር ጀምሮ በውጪ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ምሁራን የማሳተፍና ረቂቅ ሕጉን የማዳበር ሥራዎች መሠራታቸውንም አስረድተዋል ዳይረክተሩ።

ከረቂቅ ሕጉ መጀመር በፊትም በጠቅላይ ሚኒቴር ጽሕፈት ቤት በኩል በጉዳዩ ላይ ጥልቅ የምርምርና የጥናት ሥራዎች መሠራታቸውንም አቶ በላይሁን ገልጸዋል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ አቶ አዲሱ ጌትነትም ነባሩን አዋጅ ሙሉ ለሙሉ ለመተካት የተረቀቀው አዲሱ አዋጅ ከነባሩ የሚለይበትን ዝርዝር ነጥቦች ለባለድርሻ አካላቱ አስረድተዋል።

47 አንቀጾችና ሰባት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት አዲሱ ረቂቅ በሰዎች የመነገድና ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር አዋጅ በወንጀለኞች ላይ እስከ ሞት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን የያዘ አዋጅ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል።

በረቂቅ ሕጉ ላይ ውይይት ያደረጉት ባለድርሻ አካላትም ዜጎችን ከሕገ ወጥ ዝውውርና ጉልበት ብዝበዛ  ለመታደግ ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱን አድንቀው ነገር ግን ረቂቅ ሕጉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብቻ መስጠቱና በአጥፊዎች ላይ የሞት ቅጣት እንዲጣል መወሰኑን የሚጠቅሱቱ መሻሻል እንደሚገባቸው አመልክተዋል።

ተሳታፊዎቹ አክለውም በአዋጁ ላይ ከቃላት አጠቃቀም ጀምሮ ቢስተካከሉና ቢጨመሩ ያሏቸውን ነጥቦች በዝርዝር አንስተው አስተያየት ሰጥተዋል።

ከባለድርሻ አካላት ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፀረ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ግብረ ሃይል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትያ ሰይድ ማብራራያና ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለይም ግንዛቤ ማስጨበጥንና የሞት ቅጣትን አስመልክቶ ወይዘሮ ፈትያ የሚከተለውን  ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም