ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ተቀብለው አነጋገሩ

139
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15/ 2012  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መክረዋል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለአጭር ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከ20 ዓመታት በፊት የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት ሻክሮ ቆይቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደሃላፊነት ከመጡ በኋላ በሐምሌ 2010 ዓ.ም ሰላም እንዲወርድ ማድረጋቸው ይታወሳል። ለሰላም ጥረቱ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተደረሱ የሰላምና ወዳጅነት ስምምነቶችን በወቅቱ ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም