የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና የቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከልን ጎበኙ

75
አዜአ ታህሳስ 13 / 2012 ዓ.ም  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና የቴክኖሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከልን ጎበኙ። በዚሁ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያ ከሶሰት ቀናት በፊት ያመጠቀቻት ሳተላይት ስላለችበት ሁኔታ ለአባላቱ ገለጻ አድርገውላቸዋል። 'ETRSS-1' ቻይና ከሚገኝ ማምጠቂያ ማዕከል ነው አርብ ማለዳው ወደ ህዋ የመጠቀችው። ሳተላይቷ ለግብርና፣ ለደንና አየር ንብረት ጥበቃ፣ ለማዕድንና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ጥናት፣ ለመሰረተ ልማት ዝርጋታና መረጃ ለመሰብሰብ እንደምትውል ታውቋል። የሳተላይቷ ግንባታ ከቻይና ጋር በመተባበር የተከናወነ ሲሆን 20 ኢትዮጵያዊያን ኢንጂነሮች ተሳትፈውበታል። ሳተላይቷን የመቆጣጠርና መረጃዎች የመሰብሰብ ስራውም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዊያን መሃንዲሶች ይከናወናል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም