ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች በጎንደር፣ ደሴና ደብረ ማርቆስ ከተሞች እየተካሄዱ ነው

74
ጎንደር/ ደሴ/ ደብረማርቆሰ ሰኔ 16/2010 የዶክተር አብይ አህመድን የለውጥ እርምጃዎች የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፎች በጎንደር፣ ደሴና ደብረ ማርቆስ ከተሞች እየተካሄዱ ነው። በጎንደር ከተማ መካሄድ የጀመረው ሰልፍ መነሻውን መሃል ፒያሳ በማድረግ ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ አራዳ፣ ብልኮ፣ አውቶፓርኮና መሰል ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ድጋፉን እየገለፀ ይገኛል። ሰልፈኞቹ “ከወረስነው ቂም የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የለውጥ ጉዞ አንደግፋለን፤ ድል ለዴሞክራሲ " የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ። በተመሳሳይ በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ከየቀበሌው ተደራጅተው የመጡ ሰልፈኞች በተክለሃይማኖት አደባባይ ድጋፋቸውን እየገለጹ ይገኛል። እንዲሁም የደሴ ከተማ ህዝብ ለዶክተር አብይ አህመድ ያለውን ድጋፍ ለማረጋገጥ ወደ ሆጤ ስታዲዮም በመግባት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። በህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሃይማኖት አባቶችና መላው ህዝቡ እየተሳተፈ ይገኛል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም